right
እግዚአብሔርን እንዴት እንከተላለን? እግዚአብሔር እንዴት እንድንኖር ይፈልጋል?
በሕይወታችን ውስጥ፣ ዕድሜያችን እየጨመረ ሲሄድ፣ እንዴት በትክክል መኖር እንዳለብን፣ እንዴት በአግባቡ መመላለስ እንዳለብን፣ ደስታንና የሕይወትን እውነተኛ ትርጉም የት መፈለግ እንዳለብን ብዙ ጊዜ እናስባለን። በውድ ዕቃዎችም ሆነ በስኬቶቻችን እርካታ አናገኝም…
ኢየሱስ ሕይወታችንን እንደሚያድንሰምተናል። ይህ በቂ ነው ወይስ እኛ ራሳችን አንድ ነገር ማድረግ ያስፈልገናል?
መጽሐፍ ቅዱስ ከጥንት ጀምሮ የግለሰቦችንና የሕዝቦችን ጉዞ ይገልጻል፤ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ፣ ለምን እንደፈጠረንና ከእኛ ምን እንደሚጠበቅ ጥሩ ግንዛቤ እንድናገኝ ይረዳናል። ነገር ግን ከመጀመሪያው እንጀምር።
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል የሰጠንን በብሉይ ኪዳን የሚገኙትን አሥርቱን ትእዛዛት እንመልከት። አሥርቱ ትእዛዛት ከሺህ ዓመታት በፊት ለሰዎች የተሰጡ ሲሆን፣ አጭርና ቀላል ናቸው፤ እግዚአብሔር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ ማወቅ ለሚፈልጉ ጥሩ መነሻ ናቸው።