ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ

church

ለምንድን ነው ይህን ያህል ብዙ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ያሉት?

በዓለም ላይ እጅግ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት አሉ፤ እያንዳንዳቸውም የተለያዩ ወጎች፣ ሥርዓቶችና እምነቶች አሏቸው። ታዲያ የትኛውን መቀላቀል ይኖርብናል?

ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስ፣ ባፕቲስት፣ ሉተራን፣ ሜቶዲስት፣ ፕሬስቢቴሪያን… በደርዘን የሚቆጠሩ ዋና ዋና የክርስትና ቤተ እምነቶች አሉ፤ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትም በሥርዓትና በእምነት ያላቸውን ልዩነት በማጉላት ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ያርቃሉ።

እያንዳንዱ ሰው ለእርሱ ይበልጥ የሚስማማውን ቤተ ክርስቲያን እንዲቀላቀል የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መኖራቸው ለክርስትና መልካም ነውን?

በክርስቲያኖች መካከል መለያየት የጀመረው ገና በሐዋርያው ጳውሎስ ዘመን ነበር። በቆሮንቶስ ላለችው ቤተ ክርስቲያን የጻፈው ይህ ነው።