ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ

«ጠላቶቻችሁን ውደዱ» ማለት ምን ማለት ነው?

War and child crying

ባልንጀራችንን፣ ቤተሰባችንንና ወዳጆቻችንን መውደድ እንችላለን። ነገር ግን ጠላታችንን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው? በእርግጥ ማድረግ ያስፈልገናል?

44እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤5፥44 አንዳንድ የጥንት ቅጆች የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ ይላሉ። ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤
( ማቴዎስ 5:44 )

በንድፈ ሐሳብ ደረጃ እንኳ ቀላል አይመስልም፤ በተግባር ደግሞ ፈጽሞ የማይቻል ይመስላል። በእርግጥስ አስፈላጊ ነው?…

ኢየሱስ ይህን እንዴት እንደሚያብራራ እንመልከት።

44እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤5፥44 አንዳንድ የጥንት ቅጆች የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ ይላሉ። ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤ 45እንደዚህም በማድረጋችሁ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ፀሓዩን ለክፉዎችና ለመልካሞች ያወጣል፤ ዝናቡንም ለኀጢአተኞችና ለጻድቃን ያዘንባል። 46የሚወድዷችሁን ብቻ ብትወድዱ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮችስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? 47ወንድሞቻችሁን ብቻ እጅ የምትነሡ ከሆነ ከሌሎች በምን ትሻላላችሁ? አሕዛብስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? 48ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።
( ማቴዎስ 5:44-48 )

በእርግጥም ዙሪያችንን ብንመለከት ሁሉም ሰው ፀሐይንና ዝናብን፣ የሚተነፍሰውንም ንጹሕ አየር እንደሚቀበል እናያለን። እኛም ሆንን ጠላቶቻችን ትንፋሽ በሚያስቆርጡ መልክዓ ምድሮችና ግርማ ባላቸው እንስሳት በተሞላው በዚህ ድንቅ ዓለም ውስጥ ተቀምጠናል…

ጠለቅ ብለን ብንመለከት ደግሞ ጠላቶቻችን ቢያውቋቸውም ባያውቋቸውም እንደ እኛ እናትና አባት እንደነበሯቸው እናያለን። ምናልባትም ወላጆቻችን እኛን እንደወደዱን ያህል ወላጆቻቸውም እነርሱን ወድደዋቸው ይሆናል።

ከአርተር ኮናን ዶይል የሼርሎክ ሆምስ መጽሐፍ የተወሰደ አንድ ጥቅስ እነሆ፤ በዚህ ታሪክ ውስጥ አንዲት እህት የተገደለውን ወንድሟን ታለቅስ ነበር፤ እርሱም በአገሪቱ ካሉት እጅግ አደገኛ ወንጀለኞች አንዱ ሆኖ ተገኝቶ ነበር...

«ለዓለም ሁሉ እርሱ የዓመፅ ሰው፣ ግማሹ እንስሳ ግማሹ ጋኔን ነበር፤ ለእርሷ ግን ሁልጊዜም የልጅነቷ ዘመን ያ እልኸኛ ትንሽ ልጅ፣ እጇን አጥብቆ ይይዝ የነበረው ሕፃን ሆኖ ቀረ።»

ጠላታችን በእርግጥ የምንወደው ሰው ሊሆን ይችላል?

የሰማዩ አባታችን አሁን ጠላታችን ብለን በምንጠራው ሰው ውስጥ አዲስ ሕይወትን እንዴት እንደ እፍ እንዳለበት፣ በእናቱ ማኅፀን ሳለ እንዴት እንደተንከባከበው፣ ከዚያም እንዲወለድ አድርጎ በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ልብስን፣ የሚበላውን ምግብና የሚጠጣውን ውኃ እንዴት እንደሰጠው አስቡ… አሁን ደግሞ የጠፋውን ልጁን መልሶ ለማግኘት፣ እንደገና ፈገግ ሲል ለማየትና የሰማዩን አባቱን «አባዬ!...» ብሎ ሲጠራው ለመስማት በጉጉት ይጠባበቃል። እግዚአብሔር እኛን እንደሚወደን ያህል እርሱንም ይወደዋል።

ዳዊት ያለማቋረጥ ያሳድደውና ሊገድለው ይሞክር የነበረውን የጠላቱን የሳኦልን ሕይወት እንዴት እንዳተረፈ እናስታውስ።

3ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፣ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር። 4የዳዊት ሰዎችም ዳዊትን፣ “እግዚአብሔር፣ ‘የወደድኸውን ታደርግበት ዘንድ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ’ ብሎ ለአንተ የተናገረው ቀን ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም በልቡ እየተሳበ ሄዶ የሳኦልን ልብስ ጫፍ ማንም ሳያውቅ ቈርጦ ወሰደ።
5ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቍረጡ ልቡ በሐዘን ተመታ። 6ለሰዎቹም፣ “እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና እግዚአብሔር የቀባው ስለ ሆነም እጄን በርሱ ላይ ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ” አላቸው።
( 1 ሳሙኤል 24:3-6 )

ስለዚህ ጉዳይ ዳዊት ለሳኦል የተናገረው ቃል ይህ ነው፦

12እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ይፍረድ። ክፉ ስላደረግህብኝ እግዚአብሔር ይበቀልህ እንጂ፣ እጄስ በአንተ ላይ አትሆንም፤ 13በጥንት አባባል፣ ‘ከክፉ አድራጊዎች ክፉ ድርጊት ይወጣል’ እንደ ተባለ፤ አሁንም እጄ በአንተ ላይ አትሆንም።
( 1 ሳሙኤል 24:12-13 )

ጠላቶቻችንን እንዴት መውደድ እንዳለብን የሚያሳየን ሌላው ምሳሌ ራሱ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ ስለሰደቡትና ስለሰቀሉት ሰዎች ምን እንዳለ እንመልከት።

34ኢየሱስም፣ “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው”23፥34 አንዳንድ የጥንት ቅጆች፣ ይህ ዐረፍተ ነገር የላቸውም። አለ። እነርሱም ልብሱን በዕጣ ተከፋፈሉት።
( ሉቃስ 23:34 )

ይህ ደግሞ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ ሲሞት የተናገረው ቃል ነው።

54በሸንጎው ስብሰባ ላይ የነበሩትም ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ፤ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። 55እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንዲሁም ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፣ 56“እነሆ፤ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ።
57በዚህ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ጆሯቸውን ደፍነው እርሱ ወደ አለበት በአንድነት ሮጡ፤ 58ይዘውም ከከተማው ውጭ ጣሉት፤ በድንጋይም ይወግሩት ጀመር። ይህ በሚሆንበት ጊዜ በዚያ የነበሩ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በተባለ ጕልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ።
59እስጢፋኖስም እየወገሩት ሳለ፣ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ነፍሴን ተቀበላት፤” ብሎ ጸለየ፤ 60ከዚያም ተንበርክኮ በታላቅ ድምፅ፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህን ኀጢአት አትቍጠርባቸው!” ብሎ ጮኸ፤ ይህን ካለ በኋላም አንቀላፋ።
( ሐዋርያት ሥራ 7:54-60 )

እንዲህ ያለውን ታሪክ ስናነብ ራሳችንን ከአይሁድ መሪዎች ጋር አናመሳስልም። ነገር ግን በእርግጥ ኃጢአታችንን የሚገልጥብንንና የሚከሰንን ንጹሕ የእግዚአብሔር መልእክተኛ እየገደልን ያለነው እኛው ራሳችን ብንሆንስ?… እኛ ከኃጢአት የነጻን አይደለንም፤ በእኛ ላይ የተነሣውም ድምፅ ያለ ምክንያት አልመጣም።

የአይሁድ መሪዎች እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት ስታነብ በእነርሱ ላይ ምን ተሰማህ? ቁጣ፣ ንዴት ተሰማህን?… ይልቁንስ ለእነርሱ ጸጋ ቢሰማንስ? እነርሱ ትክክል ለመሆንና ሕጉን አጥብቀው ለመያዝ ይጥሩ ነበር፤ በትክክል ያላደረጉት ነገር መገለጡንም ይጠሉ ነበር። በብዙ መንገድ እኛ እንደ እነርሱ ነን፤ እነርሱም እንደ እኛ ናቸው። ስሕተታቸው ቢኖርም እንውደዳቸው። እግዚአብሔርም እንደሚወዳቸው ሁሉ ጠላቶቻችንን ለመውደድ እንሞክር።

4ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ 5ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም። 6ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም። 7ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።
( 1 ቆሮንቶስ 13:4-7 )
አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)